Wednesday, June 2, 2010

Sunday, February 7, 2010

ለሳይንቲስቱ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ መታሰቢያ

ለሳይንቲስቱ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ መታሰቢያ Print E-mail
Thursday, 09 October 2008
ለሳይንቲስቱ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ

መታሰቢያ ትሁን

በእጄ ይዤዋለሁ የናቴን መቀነት

ይተበታተነው እንዲታሰርበት

በአይምሮዬ አለ ጅማሬዬ ሁሉ

ምነው ዝም አላችሁ ሰዎች መላ በሉ

አልተኛም ነበረ እንደው በውጥን

ምንድን ነው ምክንያቱ ዝም አለኝ ወገን

ተመኝቼ ሳላይ ትውልድ ሀገሬን

እኔንም ገርሞኛአል እንዳይሆን ሲሆን

ደግ ነው ጀግና ነው አትበሉኝ እባካችሁ

እኔን ደስ የሚለኝ ሰዎች ልንገራችሁ

አንድነት አስቡ እንደኔ ሁናችሁ

አምላክም ይረዳል ከልብ ካቆማችሁ

ሀሳብ የሚጋራኝ ወንድም አጣሆ ዛሬ

ይህን ሁሉ ውጥን ጀምሬ ላህገሬ

አምጣው ያለኝ የለም ይዤው ተቀብሬ

እንዴት ያስደስታል ለሀገር መሰብ

እንዴት ያስደስታል ለወገን ማሰብ

እንቅልፍ አልነሳኝም ሆኖኛል ድባብ

እንዴት ደስ ያሰኛል ሲደክሙ ከልብ

ፍሬውን አብቦ ሲያዩት በቅርብ

የትግል ጉአዶቼ ስሙኝ ልንገራችሁ

ወደኔ ሳትመጡ አፈር ሳያቅፋችሁ

ለኢትዮጲያ ሀገሬ ከልብ ደክማችሁ

ለዚያ ለድሀ ህዝብ መከታ ሆናችሁ

ነጻነት አሳዩት እናንተ ጠፍታችሁ

ያገርሬን ትንሳኤ ወገኖቼ አሳዩኝ

አዳምጣለሁኝ ቅጣው ቅጣው በሉኝ

እኔንም ወስዳችሁ ላገሬ አፈር አብቁኝ

ዲሞክራሲ ሰፍኖ በኢትዩጲያ ምድር

መብቱ ተጠብቆ ተማሪው እንዲማር

መለያየት ቀርቶ በጀግኖቹ ሀገር

ፍቅር ሰላም ሰፍኖ በኢትዮጲያ ምድር

የተበታተነው ባንድ ላይ ሲታሰር

ይሄ ነው ምኞቴ አደራ የምላችሁ

ካኢትዮጲያ ምድር ጠላት አባራችሁ

ላገሬ አፈር አብቁኝ አደራ እባካችሁ

ችግር ተወግዶ ሲሆን አልጋ ባልጋ

ጨለማው ተገፎ ሌሊቱ ሲነጋ

ወራቱ ሲቀየር ክረምት አልፎ በጋ

ንገሩኝ አደራ እኔም ልረጋጋ

ጠላት ስልጣን ይዞ ሆኖብኝ ደንቃራ

በህይወቴ እያለሁ ላገሬ ልሰራ

አልሜ የሄድኩትን መጣሁኝ ሳልሰራ

ይህን ሁሉ ውጥን ጀምሬ ላገሬ

አምጣው ያለኝ የለም ይዤው ተቀብሬ

ወገን ይቀበለኝ ከብዶኛል ቀንበሬ

እኔ ልንገራችሁ እናንተ ስሩልኝ

ውጥኑን አፈሩ ሳያበላሽብኝ

እውነቱን ወስዳችሁ ለወገን ስጡልኝ

ይሄ ነው መልክቴ ወገን ሁሉ ስሙኝ

ከወገኖቼ ጋር አንድነት አስቡኝ

ወንድወሰን ሰብስቢ